Home
Add Document
Sign In
Register
Tesfatsion
Home
Tesfatsion
Abne Teklehaymanot...
Author:
zodiac42000
302 downloads
554 Views
202KB Size
Report
DOWNLOAD .PDF
Recommend Documents
No documents
አንዳንድ ያሰት ቄሶች - አየነ ብላችሁ ቤተስኪያናችንን - አትንኩ ባካችሁ አለንና ብዙ - ታላላቅ መምህር ክርስትያንነትን - ገልጦ ሲያስተምር “የቄሳር ለቄሳር - የእግዜርም ለእግዜር” ብሎ የሚያስረዳ - እውነቱን ነገር (ቅኔ - አቤ ጉበኛ)
የመጨረሻው የአክሱም ንጉስ ድል ናኦድ፣ ስርአተ መንግስቱ ከወደቀ በሁዋላ በዙሪያው የነበሩ ካህናትና ሊቃውንት ሁሉ እጣ ፈንታቸው ስደት ሆነ። የስደት አግጣጫቸውም ወደ ሸዋ ሆነ። ጉዞአቸው በቡድን ነበር። መቶ፣ ሁለት መቶ እየሆኑ እንደየዝምድናቸው ተቧድነው ተጓዙ። ከእነዚህ መሃል አባ ይድላ 150 ሰው ያቀፈውን ቡድን እየመሩ ወደ ሸዋ ያቀኑ ካህን ነበሩ። አማርኛ ቋንቋ የመንግስት ቋንቋ ይሆን ዘንድ በሩን የከፈተው የአባ ይድላ የልጅ ልጅ ፍስሃፅዮን ፀጋዘአብ መሆኑ ይወሳለታል። አባ ይድላ ፀጋዘአብን ወለደ። ፀጋዘአብ እግዚሃሪያ የተባለች ቆንጆ ሴት አግብቶ ለመውለድ ቢሞክርም እግዚአብሄር ልጅ ከለከላቸው። በእድላቸው እያዘኑ በፍቅር ይኖሩ ነበር ይባላል። ጊዜው 11ኛው ክፍለ ዘመን እንደመሆኑ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ የምትባል አገር ነበረች ማለት አይቻልም። የአካባቢ 240
ጉልበተኞች ራሳቸውን ንጉስ ብለው እየጠሩ የቻሉትን ያህል ይገዙ ነበር። በዚህ መሰረት ዳሞት ላይ ዙፋኑን ተክሎ ከፊል ሸዋን የሚገዛ መቶሎሚ የተባለ የወላይታ (ሃዲያ?) ጀግና ተነስቶ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን መቶሎሚ እና ወታደሮቹ እንደተለመደው በየመንደሩ እየዞሩ ባላገሩን ያስገብሩ ነበር። ፍሪዳ ያስጥላሉ። እጅ መንሻ ይቀበላሉ። ቆንጆ ሲያገኙ ይነጥቃሉ። ገበሬውን ያጉላላሉ። የተለመደው ይኸው ነበር። የመቶሎሚ ወታደሮች ዳሞትና ዙሪያውን እየዞሩ ሲያስገብሩ እግር ጥሎአቸው ፀጋዘአብና ሚስቱ ከሚኖሩባት ዞረሬ ከተባለች ቀበሌ ደረሱ። (አንዳንድ ፀሃፊዎች ‘ፀጋዘአብ’ን ‘ፀጋዛፉ’� ይሉታል። ስሙን አማራዊ ለማድረግ በመፈለግ እንጂ፣ ስሙ ፀጋዘአብ ነበር። “መለስ ዜናዊ”ን “መለሰ ዜናዊ”� እንደሚሉት ማለት ነው።)
እንደተለመደው ገበሬውን እየዘረፉ ሲያንገላቱ ፀጋዘአብ ህይወቱን ለማዳን ሚስቱን ጥሎ በመሸሽ ከሚካኤል ቤተክርስትያን ገብቶ ተሸሸገ። የመቶሎሚ ወታደሮች ቆንጆዋን ሴት ብቻዋን ሲያገኟት፣ “ቆንጆይቱ ለንጉስ ትገባለች።”�ብለው በምርኮ ይዘዋት ሄዱ። ንጉስ መቶሎሚም ወይዘሮዋን በደስታ ተቀበለ። እንደ ንግስት አልብሶ፣ ጌጣጌጥና ወርቅ ሸልሞ፣ ከእልፍኙ በማስገባት ከ12 ሚስቶቹ ሁሉ የበላይ ሚስት አደረጋት። እርግጥ ነው፣ እዚህ ላይ በርካታ አከራካሪ ታሪኮች አሉ። መቶሎሚ የፀጋዘአብን ሚስት መንጠቁ ላይ ስምምነት አለ። አብራው ረጅም ጊዜም ኖራለች። ከመቶሎሚ አስራሁለት ሚስቶች የበለጠችው ቆንጆ ይህችው ከፀጋዘአብ የተነጠቀችው እግዚሃሪያ ነበረች። እዚህ ድረስ ልዩነት የለም። የመቶሎሚ አፈታሪክ፣ “እግዚሃሪያን ሚስቱ አደረጋት።”� ይላል። አባ ዮሃንስ ከማ የተባሉ ደብተራ የፃፉት ግን፣ “ሰርግ ደግሼ ነው የማገባት ብሎ እስከ ሰርጉ 241
እለት አልነካትም።”� የሚል ነው። ዮሃንስ ከማ ትረካውን ሲቀጥል፣ “...ሰርግ በተደገሰበት እለት፣ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ከሰርጉ መሃል መንጥቆ በማውጣት ወደ ቀድሞ ባሏ መለሳት።”�ይላል። የፀጋዘአብ ሚስት ወደ ቀድሞ ባሏ መመለሷ እውነት ነው። የመቶሎሚ አፈታሪክ እንደሚለው ግን በቀሳውስት ልመናና ሽምግልና ነበር የተመለሰችው። ስትመለስም ፀንሳ ነበር። ዮሃንስ ከማ ግን ይህን አይቀበልም። “ከተመለሰች በሁዋላ ከፀጋዘአብ ፀነሰች።”� ብሎ ነበር የፃፈው። በርግጥ ፀጋዘአብ ለረጅም ጊዜ ሚስቱን ማስወለድ አልቻለም ነበር። ቢሆንም በእግዚአብሄር ፈቃድ ከፀጋዘአብ መፀነሷ እውነት ሊሆን ይችላል። ላይሆንም ይችላል። የአብርሃም ሚስት ሳራ በመጨረሻ ልጅ ማግኘት እንደቻለችው የእግዚሃሪያም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። የሆነው ሆኖ እግዚሃሪያ ከመቶሎሚ ወደ ቀድሞ ባሏ በተመለሰችበት እለት የተፀነሰው ታሪከኛ ልጅ፣ የዚህ ትረካ ትኩረት የሆነው ፍስሃፅዮን ነበር። የፍስሃፅዮን ታሪክ እጅግ አስገራሚ ነው። በተፀነሰበት እለት ቅዱስ ሚካኤል በህልም ተከስቶ ለእናቱ እንዲህ አላት፣ “ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ብዬ የነገርኩሽ በማህፀንሽ ተፀነሰ።” ይህ የቅዱስ ሚካኤል መልእክት በተመሳሳይ በህልም ለፀጋዘአብም እንደተነገረው ተፅፎአል። በርግጥ ታሪኩ ከእየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ጋር ተመሳስሎአል። በኢትዮጵያ ገድልና ታሪኮች ውስጥ በርካታ ተደጋጋሚና የተኮራረጁ ታሪኮች አሉ። (ለአብነት “ከብልቴ ፀሃይ ሲወጣ አየሁ”� እያሉ ተናገሩ የሚባሉ ሴቶች ጥቂት አይደሉም። የፍስሃፅዮን እግዚሃሪያ እና የምኒልክ እጅጋየሁ ይጠቀሳሉ። ግራኝ አህመድና ይሁዲት ጉዲት አባታቸው ዲያቆን እንደነበር ተመሳሳይ አፈ ታሪክ አላቸው። እውነት አይደለም። ጀግና የሆኑት፣ “በአባታቸው ወገን የኛ ስለሆኑ ነው።”�የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የተፈጠረ ተረት ነው።) 242
እግዚሃሪያ ወደ ቀድሞ ባሏ ስትመለስ መቶሎሚ የሸለማትን ብዙ ወርቆችና ጌጣጌጦችን ይዛ ነበር። ከፊሉን ጌጣጌጥ በመሸጥ ድሆችን አበሉ፣ አጠጡ። በመፀነሷም ከፍተኛ ደስታ ሆነ። ቀኑን ጠብቆ ፍስሃፅዮን ከተወለደ በሁዋላም ደስታቸው በእጥፍ ጨመረ። “መልኩም እጅግ ድንቅ ነው፤ እንደ ብርሌ እንደ መስታወት የሚያንፀባርቅ ነው። ቅላቱም እንደ ፅጌረዳ ነው”� ተብሎ ተፅፎአል። “ወራእዩኒ መንክር ጥቀ፣ ፀአዳ ከመ አስሃትያ፤ ወቀይህ ከመ ፅጌረዳ።”�ይለዋል ግእዙ። ፍስሃፅዮን ተአምር መስራት የጀመረው እንደ እየሱስ ክርስቶስ 30 አመት ከሆነው በሁዋላ አልነበረም። ገና አንድ አመት ሳይሞላው ማማተብና የፀሎት ቃላት ከአንደበቱ ማፍለቅ ጀመሮ ነበር። እናቱ እግዚሃሪያ በህፃኑ ድርጊት ተደንቃ በትግርኛና በግእዝ ቀላቅላ አናገረችው፣ “ፍሰሃፅዮን ወደይ (ፍስሃፅዮን ልጄ) ዝሰ ቃል ግብረ አቡከ ውእቱ። (ይህ ቃል የአባትህ ስራ ነው።) ወለከሰ ጠቢው አጥባት። (ላንተ የሚገባህ ጡት መጥባት ነው።)”� የፍስሃፅዮን የልጅነት ህይወት እጅግ የሚያስቀና እንደነበር ተፅፎአል። በመላእክት ታጅቦ ይውል ነበር። በልጅነቱ የመላእክቱን ክንፍ እየነካካ ተጫውቷል። በጣም መሳቅ ይወድ ነበር። ቃል በቃል ግእዙ፣ “ወይስህቅ ኩሉ ጊዜ!”� ይለዋል። እንደ ተራ ህፃናት አልቅሶ አያውቅም። አርባ ቀናት ሞልቶት ለጥምቀት ቤተክርስትያን በወሰዱት ጊዜም ስሙን “ፍስሃፅዮን”� ብለው ጠሩት። በዚያን ሌሊት ግን ቅዱስ ሚካአል በህልም ተገለልጦ፣ ፀጋ ዘአብን እንዲህ አለው፣ “ስሙ ፍስሃፅዮን አይደለም።” “ጌታዬ! ስሙ ማነው ታዲያ?”�ሲል ጠየቀ ፀጋዘአብ። “ስሙን ልነግርህ አልተላክሁም።”� አያያዘናም ቅዱስ ሚካኤል አከለበት፣ “...ይህ ህፃን በተረገዘ ጊዜ በህልም ያየኸውን ግን ልተረጉምልህ ታዝዣለሁ።” “በል ጌታዬ! ተርጉምልኝ።” “ፀሃይ ከቤትህ ሲወጣ ያየኸው ከአብራክህ የተከፈለ ይህ ልጅ 243
ነው። አህዛብ ይገዙለታል። የሁሉም መጠጊያ ይሆናል። ከነገስታቱ በላይ ሆኖ ይኖራል። ተአምራቱ ከዛፍ ፍሬ ይበዛል። ስሙም ለዘልአለም ሲመሰገን ይኖራል።”������������������������ *** እነሆ! ፍስሃፅዮን አደገ... አንድ አመት ከሶስት ወር ሆነው። የመጀመሪያውን አስገራሚ ተአምር መስራት የጀመረውም በዚህ እድሜው ነበር። በሸዋ ረሃብ ገብቶ ነበር። የቅዱስ ሚካኤል በአል ደግሞ ደረሰ። የፍስሃፅዮን ወላጆች በቤታቸው ምንም የሚቀመስ እህል አልነበራቸውም። ፀጋዘአብ እህል ለማግኘት ቤተክርስትያን ሄዶ መፀለይ ጀመረ። እግዚሃሪያ ደግሞ ከቤቷ ደጃፍ ላይ ተቀምጣ፣ “ምን ይሻላል?”� እያለች ታለቅስ ነበር። በዚህ ጊዜ ህፃኑ ፍስሃፅዮን በእናቱ እቅፍ ላይ እንዳለ በጣቱ የእናቱን እንባ ጠረገላት። እናቱ ግን ይህን አላስተዋለችም። ርቦታል ብላ ገምታ ጡቷን አጎረሰችው። ህፃኑ ግን መጥባቱን ትቶ፣ “ወደ ቤት አስገቢኝ”� አይነት በምልክት አስቸገራት። እምቢ ስትለው ማልቀስ ጀመረ። “ይሄ ልጅ ምን ፈልጎ ነው?”� ብላ ይዛው ወደ ውስጥ ገባች። ጥቂት የስንዴ ዱቄት በእንቅብ ነበር። ህፃኑ ፍስሃፅዮን በእጁ ዱቄቱን አመለከታት። “እንቅቡን ስጪኝ”�ማለቱ ነው በሚል አቀረበችለት። ህፃኑ እጁን ዱቄቱ ውስጥ ጨመረው። ወዲያው ዱቄቱ እንቅቡን ሞልቶ ፈሰሰ። በዚሁ መንገድ የቅቤ እቃውን፣ የጨው ቅሉን፣ ጋኑን፣ በጠቅላላ በቤት ውስጥ የሚገኝ እቃ ሁሉ በምግብ ተሞላ። በከባዱ ረሃብ ጊዜ የአካባቢው ህዝብ ሁሉ በረሃብ ሲረግፍ የፀጋዘአብ ቤተሰብ ልጃቸው በሰራው ተአምር ምክንያት አንዳችም ችግር ሳይገጥማቸው የረሃቡን ጊዜ ተሻገሩት። (እርግጥ ነው የመቶሎሚ አፈታሪክ ይህን ትረካ አይቀበልም። መቶሎሚ “ፍስሃፅዮን ልጄ ነው”� ብሎ ያምን ስለነበር እህሉን ማሩንና ቅቤውን በድብቅ ይልክላቸው ነበር። ፀጋዘአብ ግን ይህ እንዳይታወቅበት ህፃን ልጁ ተአምር እንደሰራ ለመንደሩ ሰዎች ሁሉ ይናገር ነበር”� ይላሉ። ግራና ቀኙን መስማቱ ለግንዛቤ ይጠቅማል 244
በሚል እንጂ፣ የመቶሎሚ አፈታሪክ የፍስሃፅዮንን የልጅነት ተአምራት አይሽረውም።) የፍስሃፅዮን የልጅነት ገድል መልከ ብዙ ነው። አንድ ጊዜ አገረ ገዢው በፀጋዘአብ ቤት በኩል ሲያልፍ እግዚሃሪያን፣ “ምሳ ካለሽ አብይኝ። ርቦኛል።”�ይላታል። “ምሳ አለኝ። መጠጥ ግን የለኝም።”�ትለዋለች። “ያለሽን አምጪ።” የፀጋዘአብ ሚስት የሚጠጣ ስላልነበራት እያዘነች የምግብ ገበታ እንዲሰራ ገረዷን አዘዘች። ምግብ እየቀረበ ሳለ እግዚሃሪያ ልጇን አቅፋ ወደ ውሃ እቃው ስትጠጋ በዚያችው ቅፅበት ውሃው ወደ ጠላ ተቀየረ። ይህም እየሱስ ክርስቶስ ውሃውን ወደ ወይን ከመለወጡ ጋር የሚመሳሰል ተአምር ነበር። እግዚሃሪያ ልጇ በፈፀመው በረከት ተደስታ እንግዳውን በምግብ ብቻ ሳይሆን፣ በመጠጥ ጭምር አስተናግዳ ሸኘችው።”�ሲል ይተርካል የፍስሃፅዮን ገድል። ፍስሃፅዮን በሰባት አመት እድሜው ዳዊት ተማረ። ብሉይና ሃዲስ ኪዳንንም አጠና። በ16 አመቱ ድቁና ተቀበለ። ከዚያም ካህን ሆኖ ተሾመ። Elaine Murray Stone: A saint and his lion, The story of Tekela of Ethiopia በሚለው ለህፃናት ባዘጋጀችው መፅሃፏ የፍስሃፅዮንን ገድል ተርካለች። የኢሌይን ሙራይ ትረካ እንዲህ ይላል፣ ወጣቱ ፍስሃፅዮን ክርስትናን ለማስተማር ከቤቱ ወጥቶ እያነከሰ ወደ ጫካ ተጓዘ። በጉዞ ላይ ሳለ ታዲያ በጫካ ውስጥ አንድ አንበሳ ተሰብሮ ሲያቃስት ያገኘዋል፣ “አዬ! አንተም እንደኔ ተጎድተሃል?”�በማለት የአንበሳውን እግር በጨርቅ አሰረለት። የሚጠጣ ውሃ አምጥቶም ሰጠውና መንገዱን ቀጠለ። ይህ ከሆነ ከብዙ አመታት በሁዋላ አንበሳውና ፍስሃፅዮን ተገናኙ። አንበሳውም የረዳውን ጓደኛውን ስላገኘ ደስ ብሎት፣ “ባንተ ደግነት የዳነ እግሬ አንተን ያገለግላል።”� አለውና 245
ለፍስሃፅዮን ፈረስ ሆነለት። ፍስሃፅዮንም መስቀሉን ይዞ አንበሳ እየጋለበ በሸዋ ምድር ሰበካውን ቀጠለ። የሸዋ ሰዎችም አንበሳውን በመፍራት ክርስትያን ለመሆን ፈቀዱ። (ይህ የኢሌይን ተረት ፍስሃፅዮን ሰባት አመት በአንድ እግሩ ቆሞ ከመፀለዩ በፊት አንካሳ እንደነበር የሚጠቁምና ከገድሉ ጋር የሚጋጭ ነው። ለማመሳከር እንዳይቻል ግን ኢሌይን ሙራይ የትረካ ምንጯን አልገለፀችም። “ይነጋል”� በሚል ርእስ መፅሃፍ ያሳተመው ዲያቆን ፅጌ ስጦታው ግን የተለየ ታሪክ ያቀርባል። ፍስሃፅዮን እግሩን ያጣው በጦርነት በጎራዴ ተመትቶ መሆኑን ይገልፃል።) *** ፍስሃፅዮን ሚስት አግብቶ መኖር ጀምሮ ነበር። ሚስቱ ከመውለዷ በፊት ግን ሞተችበት። እናትና አባቱም ተከታትለው ሞቱበት። ከዚህ በሁዋላ ፍስሃፅዮን ስሙን ቀየረ። ተክለሃይማኖት ተብሎ ሙሉ ጊዜውን በሃይማኖት ጉዳይ ላይ አዋለ። እዚህ ላይ የመቶሎሚና የአቡነ ተክለሃይማኖት የዝምድናና የግንኙነት ምስጢር ተሸፋፍኖ ቀርቶአል። ከአፈ ታሪክ በቀር የተፃፈ መረጃ የለም። በርግጥ መቶሎሚ አቡነ ተክለሃይማኖትን በቆዳ ጠቅልሎ በንብ ቀፎ ውስጥ ከትቶ ወደ ገደል ወርውሮት እንደነበር በገድሉ ላይ ተፅፎአል። ፍስሃፅዮን ግን ምንም ሳይሆን በተአምር ከገደል ወጥቶ እንደገና ንጉሱ ፊት ቀረበ። መቶሎሚ መልሶ ከነተከታዮቹ ወደ ገደል አስወረወረው። እንደገና ፍስሃፅዮን ምንም ሳይሆን ተመልሶ ወደ ንጉሱ መጣ። መቶሎሚ በዚህ ተበሳጭቶ ፍስሃፅዮንን ለመግደል ጦሩን ሲወረውርበት፣ ጦሩ የመቶሎሚ እጅ ላይ ተጣብቆ ቀረ። የተጣበቀውን ጦር ለማስለቀቅ የተቻለው ፍስሃፅዮን ከፀለየለት በሁዋላ ነበር። ከዚያም መቶሎሚ ክርስትናን ተቀብሎ ስሙን ወደ ፍስሃፅዮን ቀየረ። የመቶሎሚ አፈታሪክ ግን ከዚህ በተቃራኒው ያወጋል። 246
መቶሎሚ ከእግዚሃሪያ የወለደውን ልጅ ዝና ለመጨመር ሲል ወደ ገደል የመወርወሩን ድራማ እንዳዘጋጀ ይተርካሉ። መቶሎሚ ስሙን ወደ ፍስሃፅዮን መቀየሩም ለልጁ ባለው ፍቅር የተነሳ እንደሆነ ያምናሉ። ለፍስሃፅዮን ዝና መጨመር የመቶሎሚ ስውር ሚና ከፍተኛ እንደነበር የሚገለፀው ትረካ ግን በኦርቶዶክስ ካህናት ዘንድ ተቀባይነት የለውም። *** የዳኛቸው ወርቁ “አደፍርስ”� የተባለው ልቦለድ ድርሰት ከጊዜው ቀድሞ የፈነዳ አብዮት ነበር ማለት ይቻላል። አቡነ ተክለሃይማኖትን በመቃወም ጠንካራ ሂስ የሰነዘረ መፅሃፍ በመሆኑ “አደፍርስ”� ገበያ ላይ ብዙ አልቆየም። በንጉሳዊው ስርአት ስላልተወደደለት ዳኛቸው እራሱ ኮፒውን ከየሱቁ ሰብስቦ ዘጋበት። በመሆኑም የዳኛቸው ወርቁ፣ “አደፍርስ”� በቅጡ የመነበብ እድል አላገኘም። በትረካው ውስጥ ዋናው ገፀባህርይ አደፍርስ እና አባ ዮሃንስ የተባሉ ቄስ እንዲህ ሲያወጉ ይነበባሉ፣ “...አቡነ ተክለሃይማኖትን ፃድቅ ሊያሰኛቸው የቻለው ምንድነው? ደብረሊባኖስን አቅንተው ገዳም ስላደረጉ?”� ሲል ጠየቀ አደፍርስ። “ተክለሃይማኖት የፃድቅ ፃድቅ ናቸው። መቶሎሚን የመሰለ የወላሞ አረመኔ ንጉስ ወደ በጎ ምግባር መልሰው አጥምቀው ክርስትያን ያደረጉ። ሰባት አመት ሙሉ በአንድ እግራቸው ቆመው ስለ ሃገር ስለ ህዝብ ሲፀልዩ የቆሙበት እግራቸው እስከ መቆረጥ የደረሰ፤ ስድስት ክንፎች እስከ ማብቀል ድረስ ክብር የተሰጣቸው፤ ፃድቅ ናቸው...” “እኔ የምለው ስለ ክርስቶስ ሲሉ አልተሰቃዩም ነው...” “በቆዳ እየተጠቀለሉ እገደል እስከመወርወር፤ እባህር ውስጥ ከመጣል የበለጠ መሰቃየት አለ?” “እገደል ተወርውረዋል? እባህር ተጥለዋል ነው የሚሉኝ?” “እንዴታ! ምንም ሳይሆኑ ወጥተዋል።” “ስድስት ክንፎች አውጥተው ነበር ነው የሚሉኝ?” 247
“እንዴታ! እቁርጭምጭሚታቸው ላይ ያለው ሳይቆጠር...” “እስከሱ ስምንት መሆኑ ነው?” “አይ ገድላቸው ስምንት አይልም። ስድስት ነው። ምስላቸው ላይ በግልፅ ልታየው ትችላለህ። እግራቸው ክንፍ አጎጥጉጦ ይታያል።” (ርግጥ ነው፤ ፍስሃፅዮን ከደብረዳሞ ገዳም በገመድ በመውረድ ላይ ሳለ ገመዱ ተበጥሶበት፣ በተአምር ስድስት ክንፍ አብቅሎ፣ አንድ ኪሎሜትር ያህል እንደ አሞራ በመብረር ሜዳው ላይ ማረፉ መወራት የጀመረው ገና በህይወት ሳለ ነበር። “ይህን ተአምር በአይናችን አይተናል።”� የሚሉት የደብረዳሞ ቄሶች ናቸው። ፍስሃፅዮን ግን ይህንን እንዳልተቀበለው ተፅፎአል። ከዚህ ወሬ በሁዋላ፣ ወሬውን በመጥላቱና በሙገሳው ባለመደሰቱ፣ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርጉለትም እንኳ ወደ ደብረዳሞ ተመልሶ ለመሄድ ሳይፈቅድ ቀርቶአል።) የዳኛቸው ወርቁ የአደፍርስ ትረካ እንዲህ ሲል ይቀጥላል፣ “አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስስ? ግብፃዊ ናቸው መባሉ?” “ግብፃዊስ ግብፃዊ ናቸው። ብቻ ቢሆንም በመላ ኢትዮጵያ የታወቁ ፃድቅ ናቸው።” “የአገራችን ፃድቃን መች አነሱንና ነው ታዲያ ...ካሉ ማለቴ ነው...በሰው አገር ፃድቃን የምናምነው?” “ካሉ አትበል ወዳጄ! ሞልተዋል። እነ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ እነ አቡነ መልከፀዴቅ፣ እነ ወለተ ጴጥሮስ፣ እነ ዘርአብሩክ፣ እነ ተክለ አልፋ፣ እነ ሃራ ድንግል፣ እነ መብአ ፅዮን፣ እነ አቡነ ፊሊጶስ፣ እነ አቡነ ተክለሃዋርያት....” “ሸዋዎች መሆን አለባቸው መቼም እነዚህ ሁሉ ቅዱሳን?” “ሸዋዎች? ሸዋ፣ ግብፅ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ሮም አይልም ቅድስና። እንደ እንጉዳይ ነው የእግዚአብሄር ፀጋ በወረደበት ቦታ ሁሉ የሚወርዱት።” “ከወሎ፣ ከአርሲ፣ ከባሌ የሉባቸውም ብዬ ነው...” (ዳኛቸው ይህን የመሰለ የሰላ ሂስ በመፅሃፉ ከሰነዘረ በሁዋላ 248
በህይወት መቆየት የቻለው መፅሃፉ ስላልተነበበ፣ አሊያም ዳኛቸው የሸዋ አማራና ኦርቶዶክስ በመሆኑ “የኛው ልጅ ተሳሳተ”� በሚል ችላ ብለውት ሊሆን ይችላል። መፅሃፉን የፃፈው ላፒሶ ዲሌቦ ቢሆን ኖሮ ጉዳዩ ፖለቲካዊ መልክ መያዙ የማይቀር ነበር። *** የአቡነ ተክለሃይማኖት የህይወት ታሪክ አከራካሪ እንደሆነ እስከዘመናችን ዘልቆአል። የእኒህ ካህን ታሪክ አከራካሪ ለመሆን የበቃው ከይኩኖ አምላክ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት መነሳት ጋር ተያያዞ ፖሊቲካዊ መልክ በመያዙ ሊሆን ይችላል። (አቡን ተክለሃይማኖት አባ እየሱስ ሞአ ከሚባሉ ሰው ጋር ተመካክረው የዛጉዌ ዘር ወደሆነው ንጉስ አፄ ነአኩቶለአብ ሄዶ መንግስቱን ለሸዋ እንዲለቅ ተደራድሮታል። ስልጣን ወደ ሰለሞናውያን አንዲዛወር፣ አማርኛ ቋንቋ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆን በማድረጉ፣ ስልጣን ከይኩኖ አምላክ ዘር እንዳይወጣ የይኩኖ አምላክን የትውልድ ሃረግ ከሰለሞን ሃረግ ጋር በማያያዝ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ በማድረጉ፣ ለዚህ ፖለቲካዊ ውለታው የአክሱም ሊቀ ካህናት ይዞታ የነበረው ሁሉ ለፍስሃፅዮነን እንዲሰጥ ተደርጎአል። ለዚህ ሁሉ ድምር ውለታ በተክለሃይማኖት ስም ታቦት እንዲቀረፅለት በአፄ ይስሃቅ ዘመን ተወሰነ። ፍስሃፅዮን ወይም አቡነ ተክለሃይማኖት በ99 አመታቸው 1274 ላይ ማረፋቸውን ገድላቸው ይጠቁማል። አስከሬናቸው ደብረሊባኖስ ያረፈ ሲሆን፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አማኞች ዛሬም ድረስ ስማቸውና ቅድስናቸው ተአምራት መሰራት መቀጠሉን ያምናሉ። አማርኛ ቋንቋ እንዲስፋፋ መሰረቱን የጣለው ፍስሃፅዮን ሲሆን፤ በዚያን ዘመን አማርኛ በአማራ ሳይንት አካባቢ የሚነገር አናሳ ቋንቋ ነበር።)
ከዳኛቸው ወርቁ በመቀጠል አቡነ ተክለሃይማኖትን በግንባር ቀደምትነት የተቹ ሁለት ደፋር ብእረኞች ብቅ ብለው ነበር። ፅጌ ስጦታው እና በእውቀቱ ስዩም። በአጋጣሚ አሁንም ሁለቱም ብእረኞች 249
አማራና ኦርቶዶክስ በመሆናቸው አጃንዳው እንዳይጋነን አድርጎታል። በርግጥ ከዳኛቸው ወርቁ “አደፍርስ”� በሁዋላ አቡነ ተክለሃይማኖትን የተመለከተ ፅሁፍ ያስነበቡን እነዚህ ሁለቱ ብእረኞች ለፈፀሙት ድፍረት ዋጋ ከፍለውበታል። ፅጌ ስጦታው ለህይወቱ ሰግቶ እስከመሸሸግ ደርሶአል። በእውቀቱ ስዩም “አዲስ ጉዳይ”� በተባለው መፅሄት ላይ በፃፈው መጣጥፉ ሰበብ በቡጢ ተደብድቦ የከንፈር መሰንጠቅ እና የጥርስ መነቃነቅ ጉዳት ደርሶበታል። እምነትን በተመለከተ ለህዝብ የማይገለፁ በርካታ እውነቶች መኖራቸውን መካድ አይቻልም። እውነቱ የማይገለፀው ህዝብ ከእምነቱ እንዳይሰናከልና ሃይማኖት ፈርሶ ስርአት አልበኛነት እንዳይነግስ በማሰብ ነው። ዴሞክራሲ ባልሰፈነበት እና የህግ የበላይነት ባልተከበረበት አገር በርግጥም ስጋቱ ተገቢ ስጋት ነው። የክርስትና እምነትን በኮሌጅ ደረጃ የተማሩ ሰዎች ዲግሪያቸውን በሚቀበሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ብዙውን ጊዜ እምነታቸውን እንደሚያጡ ይሰማል። ይህ ሁኔታ፣ “እምነት በየዋህነት እንጂ በምርምር አይሆንም።”� የሚለውን አባባል እውነትነት ያጠናክረዋል። የእምነት ጉዳይ መንገዱ አንድ ብቻ ነው ማመን። በመጨረሻ አቡነ ተክለሃይማኖትን በተመለከተ አንድ መሰረታዊ ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። እየሱስ ክርስቶስ በውሃ ላይ መራመዱን ካመንን፣ ፍስሃፅዮን ስድስት ክንፍ ማብቀሉን የማናምንበት ምን ምክንያት አለ? የአቡነ ተክለሃይማኖትን የፃድቅነት ገድልና ተአምራት ተጠራጥረን፤ የእየሱስ ክርስቶስን ማመን የሚቻል አይመስለኝም። ምክንያቱም ተአምራትን በጠቅላላ ሳይንስ አይቀበላቸውም። ሰው በውሃ ላይ ሊራመድ አይችልም። በተመሳሳይ ሰው በተፈጥሮው ክንፍ ሊያበቅል አይችልም። ሳይንስ ተጨባጭ ነው። እምነት ላይ አይናችንን ጨፍነን የመቀበል ግዴታ አለብን፤ ወደድንም ጠላንም። አቡነ ተክለሃይማኖት ስድስት ክንፍ ማብቀላቸውን መጠራጠር ከጀመርን ጥርጣሬያችን ማቆሚያ አይኖረውም። ሙሴ ከግብፅ ወደ እስራኤል የተጓዘበት መንገድ በየት በኩል ነው? መፅሃፍ 250
ቅዱስ “ባህሩን በዱላ ሰንጥቆ ወደ ሲናይ በረሃ ተሻገረ።”� ብሎናል። የመፅሃፍ ቅዱስ ታሪክ ተመራማሪዎች ደግሞ “ታሪኩ የተፈፀመው ስዊዝ ካናል ከመከፈቱ በፊት እንደመሆኑ መሬት ለመሬት ተጉዞ ከግብፅ ወደ እስራኤል መሻገሩን ስብርባሪ ሸክላዎችን በመመርመር በጥናት አረጋግጠናል።”�ይላሉ። የትኛውን እንመን? አማኝ የሆነ ሰው ፈላስፎች ወይም ታሪክ ተማራማሪዎች የፃፉትን ለመስማት አይችልም። የፍስሃፅዮን ክንፍ ማብቀል ከዚህ የተለየ አይደለም። የዝቋላው አቡየ ፃድቁ ለተጠማች እርግብ (ቁራ?) አይናቸውን አፍስሰው ውሃ አጠጥተዋታል። ልጅ እያለን፣ “አቡየ ፃድቁ፣ በዘንጋቸው ወግተው ውሃ የሚያፈልቁ!”� እያልን እንዘምር ነበር። አቦ የዝቋላ ነዋሪ በነበሩበት ዘመን አድአ ላይ የውሃ ችግር አልነበረም። ዝቋላ ተራራ ላይም ሃይቅ አለ። ስለዚህ ያቺ እርግብ ክንፍ ስላላት ውሃ ሊጠማት አይችልም ነበር። የውሃ ችግር ተከስቶ ነበር ቢባል እንኳ፣ “አቡየ አይናቸውን ከሚያፈሱ፣ በዘንጋቸው መሬቱን በመውጋት ውሃ ለምን አላፈለቁም?”� ብለን አልጠየቅንም። ምክንያቱም እምነትና ጥያቄ አብረው አይሄዱም። መጠየቅ የጀመረ መጨረሻው እምነቱን በማጣት ይጠናቀቃል። ምርጫው ሁለት ነው። ሶስተኛ የለውም። ማመን ወይም አለማመን። ሼክስፒር፣ “መኖር አለመኖር ይሄ ነው ጥያቄው”� ብሎ ነበር። በዚህ አባባል ላይ መንግስቱ ለማ የቋጠሩትን አንድ ግጥም ገልብጠን እናዚማት ይሆን? “ማመን አለማመን”�ብሏል ሼክስፒር ምነው ባገኘሁት እነግረው ነበር ካለማመን ማመን ሳይሻል አይቀርም በማመን ተስፋ አለ ባለማመን ምንም
251
��������������������������������������������������������������������������� ��������������������������������������������������������������������������������� �����������������������������������������������������
×
Report "Tesfatsion"
Your name
Email
Reason
-Select Reason-
Pornographic
Defamatory
Illegal/Unlawful
Spam
Other Terms Of Service Violation
File a copyright complaint
Description
×
Sign In
Email
Password
Remember me
Forgot password?
Sign In
Our partners will collect data and use cookies for ad personalization and measurement.
Learn how we and our ad partner Google, collect and use data
.
Agree & close